በቴክሳስ ጠቅላይ ግዛት በቪክቶሪያ ከተማ መሰጊዳቸው ለተቃጠለባቸው ሙስሊሞች በከተማዋ የሚገኘው የአይሁድ ምኩራብ በሩን ከፈተላቸው፡፡ እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በቪክቶሪ ቴክሳስ የሚገኘው እስላማዊ ማዕከል (መስጊድ) ቃጠሎ ደርሶበት ነበር፡፡ ይህንን የተመለከቱ በከተማው የሚገኘው የአይሁድ ማኅበረሰብ አባላት የአምልኮ ቦታቸውን ለሙስሊም ወገኖቻቸው መሰብሰቢ እንዲጠቀሙበት የምኩራባቸውን ቁልፍ ሰጥተዋቸዋል፡፡ “አሁን ያገኘነውን ዓይነት ዕርዳታና ድጋፍ አናገኝም ብዬ […]
↧